Psalms 98

የዓለም ሁሉ ዳኛ

መዝሙር።

1 ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ አቅርቡ፤
እርሱ ድንቅ ነገሮችን አድርጓልና፤
ቀኝ እጁ፣ ቅዱስ ክንዱም
ማዳንን አድርገውለታል።
2 እግዚአብሔር ማዳኑን አሳወቀ፤
ጽድቁንም በሕዝቦች ፊት ገለጠ።
3ለእስራኤል ቤት ምሕረቱን፣
ታማኝነቱንም ዐሰበ፤
የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ፣
የአምላካችንን ማዳን አዩ።

4ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤
ውዳሴን አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፤
5 ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት፤
በበገናና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩለት፤
6በእንቢልታና በመለከት ድምፅ፣
በንጉሡ በእግዚአብሔር ፊት እልል በሉ።

7ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ፣
ዓለምና የሚኖሩባትም ሁሉ ያስገምግሙ።
8ወንዞች በእጃቸው ያጨብጭቡ፣
ተራሮችም በአንድነት ይዘምሩ፤
9እነዚህ በእግዚአብሔር ፊት ይዘምሩ፤
እርሱ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤
በዓለም ላይ በጽድቅ፣
በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል።
Copyright information for AmhNASV